መታጠቢያዎች Face wash (አንዱን መርጠሽ ሞክሪ)

ጥያቄ፡ ሶስቱ ከመሰረታዊ ሁሉም ሰው እንዲጠቀማቸው የሚመክሩት የፊት እንክብካቤ/ስኪንኬር ነገሮች ምንደን ናቸው? 

መልስ፡ 1) መታጠቢያ 2) ሞይስቸራይዘር ክሬም  3)ጸሃይ መከላከያ /ሰንስክሪን  

ክሌንሰር / መታጠቢያ Facewash በቅናሽ

CeraVe እና Cetaphil በሚሉ ብራንዶች ፊትሽ ደረቅ ነው ወይንስ ወዛማ እያሉ የሚሸጡልሽ cleanser አይነቶች አሉ። ውድ ናቸው

 

የሚጠቀሟቸው መዳሞች እና ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ እነዛ ለምሳ 3000-5000 ብር ሲያወጡ ርካሽ ነው እያሉ ቲክቶክ ሺዲዮ ለሚሰሩት ምንም ላይሆን ይችላል። ነጋዴዎቸ ደግሞ በተቻላቸው ትርፍ ሊሰሩብሽ ሲፈልጉ ሌላ አማራጭ የሌለ አስመስለው ይህን ይሸጡልሻል። ወይንም ያለዉን አማራጭ ሊያጣጥሉብሽ ይችላሉ። እንዳትሰሚያቸው

 

እንደዉም በሴራቪ መታጠቢያ ፊታቸው የተበላሸባቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ፊት ያበላሻል እያልኩኝ ሳይሆን እንደተጠቃሚው ፊት አቀባበል ይወስናል። ሌላው ሚያስፈራው ነገር ደግሞ ዱባይ ላይ ተመሳስሎ የተሰራ ፌክ ውስጡ ምን እንዳለ የማይታወቅ በሴራቪ ብራንድ ይሸጣል። ነጋዴአታውቅም ብሎ ፌኩን ኦሪጅናል ነው ብሎ ቢሸጥልሽስ ትርፍ ስለሚያስገኝለት አይታወቅም

ከሴራቪ የተሻሉ አማራጮች አሉ
ከዝህ ስር ያሉትን እይ እና ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነሽ ከአማዞን ማግኘት ትችያለሽ ሌላም ምታገኚበት ሀሳብ ከታች ሰጥሻለሁ አንብቢው

🫵 አማዞን አጠቃቀም ካላወቅሽ ጠይቂኝ

1ኛ

ሊንክ 👉   https://amzn.eu/d/0hIYQxgW

2ኛ

ሊንክ 👉   https://amzn.eu/d/0awCo0qr

3ኛ

ይቅርታ ይህን በ ሴራቪ ሳላሲሊክ አሲድ ክሌንሰር ምተክ ብቻ ነው ምትገዠዉ። በየቀኑ ለመጠቀም አይሆንም። ቀርፋች እና ለብጉር የሚሆን ሳላሲሊክ አሲድ አለበት

ሊንክ 👉   https://amzn.eu/d/06H4px4Z

4ኛ

ሊንክ 👉   https://amzn.eu/d/0bRWSwfd

ይሄ መታጠቢያ ሳሙና አይነት ሳይሆን መታጠቢያ ዉሃ ነው። በዉሃው ፊትን መወልወያ ነው። እንደሌሎቹ አረፋ የለዉም ግን በደንብ ያጸዳል። በተለይ ሜካፕ እና ሰንስክሪን የሸፈነዉን ቆዳ በዚህ አጽድቶ ከዛ በሌላ ፎም ባለው ሳሙና (እዚህ እንዳሉት ሌሎቹ አማራጮች ማለት ነው) መታጠብ ይቻላል። ከተፈለገም ይህን ብቻ መጠቀም ይቻላል። እንደዉም አንዳንዴ የጭንቅላት/ጸጉር ስር ዘይት ማስወገጃ ሁሉ አድርገው ይጠቀሙታል። በቅርቡ ታዋቂ የሆነ ማጽጃ አይነት ነው። ብቻዉን ምትጠቀሚ ከሆነ ፊትሽን በዝህ ከወለወልሽ በኋላ ማለቅለቅ አይጠበቅብሽም

ዜሮኛ - ውድ እና ፎርጅድ የበዛበት

ሴራቪ CeraVe-   ዋጋዉ 70 ድርሃም - ሊንኩን የማልሰጥሽ እንድትገዢው ስለማልመክርሽ ነው ደግሞም በየቦታው ታገኚዋለሽ ፎርጅድ እንዳይሆን ተጠንቀቂ

እዝህ ጋር ከእነዝህ ሁለቱ በተጨማሪ SA Cleanser የሚል ሳላሲሊክክ አሲድ ሚባል ለብጉር ሚሆን BHA ቆዳ ቆርፋጅ መድሀኒት ያለበት መታጠቢያም ግዥ ይሉሻል። ይህ መታጠቢያ በሳምንት አንድ ግዜ ወይንም ቢበዛ ሁለቴ ብቻ ነው ሚመከረው። ለቀሪው ቀናት ሌላ ከላይ ካሉት ውስጥ አንዱን ጨምረሽ መግዛት ሊኖርብሽ ነው። በድምሩ ለመታጠቢያ ብቻ 150 ድርሀም ልታወጭ ነው። ይህን ነገር እንደውም አንዳንዴ ሳይነግሩሽ ዝም ይሉና SA cleanser ብቻ ከተጠቀምሽ ተበላሸሽ ማለት ነው። ብዙ ሰዎች እንደዉም አለርጂክ ናቸው ለሳላሲሊክ አሲድ።  እኔ ምመክርሽ ሌላ ሁልግዜ ምትጠቀሚው ዴይሊ/ጀንትል ክሌንሰር ተጠቅመሽ ለሚያስፈልግሽ ግላዊ ፍላጎት ሌላ አክቲቭ ሚቢሉ ክሬም/ሴረም (ለቅርፈታም ይሁን ለብጉር) ለብቻው መጠቀም ነው

ሰርፕራይዝ

Day to Day ሱፐርማርኬት ርካሽ ከ5-15 AED – በእዝህ ምስል ምሳሌዎች አሉ። ዴይ ቱዴይ ወይንም ሌላ አነስተኛ ሱፐርማርኬት አጠገብሽ ካለ ቼክ አድርጊ፣

 

እኔ እዝህ አማዞን ያሉትን አማራጮች ከስር በፃፍኩት መረጃ መሰረት አንድ ወይም ሁለት መርጠሽ ግዢ። ስትጠቀሚ ቆዳሽ ከተቆጣ ሌላ ቀይሪ ሚስማማሽን እስክታገኚ

 

 

ፊሊፒኖ ሱፐርማርኬት ብትሄጅም በርካሽ ከ8 እስከ 15 ድርሃም የሚሸጡ አሉ። አሁን ግን እኔ ከዝህ በማሳይሽ አማዞን ላይ ቤትሽ ድረስ ያለዴሊቨሪ ክፍያ ያደርሱልሻል። የተመቸሽን ምረጭ እና Add to Cart ሚለው ጨምረሽ በኋላ አንድ ላይ ከሌሎቹ ጋር አብረሽ ታዥዋለሽ

ማስጠንቀቂያ

Salicylic acid ወይንም Benzoyl peroxide ወይንም Acne የሚል ካለበት ለብጉር እና ቆዳ መቀርፈቻ መዳኒት ስለሚኖረው በየቀኑ ለመጠቀም አይሆንም። Daily cleanser/face wash እና Gentle cleanser የሚለውን መርጠሽ ግዢ ብዙ አይነት አለ

መደምደሚያ

ከዝህ ስር እንደምንረዳው ከሰንስክሪን አንጻር ሴራቪ  መታጠቢያ በሚይዘው ብዛት ዋጋው ሲሰላ ከላይ ካሉት አማራጮች ጋር ተቀራራቢ ቢሆንም ፣ ሁላችንም በአንድ ግዜ 70 ድርሃም አወጥተን መጠቀም ይከብደናል። ሰንስክሪን እና ሞይስቸራይዘር ክሬም ብሎም መድሃኒት ስትጨምሪበት ከ300 መቶ ድርሃም በላይ በአንዴ ከፍሎ መሄድ ሚያዋጣ አይመስለኝም። አዛላቂ አይደለም ደግሞም አማርጠስሽ መጠቀም የሚስማማሽን ለማግኘት አያመችም። ድንገት ሴራቪ ባይስማማሽ ኪሳራው ብዙ ነው። ነገር ግን ከ10-20ድርሃም አካባቢ ዋጋ ያላቸው መታጠቢያዎች Day to Day ዴይ ቱ ዴይ ሱፐርማርኬት እና ፊሊፒኖ ሱፐርማርኬቶች ታገኛለሽ። መታጠቢያ፣ እና ሞይስቸራይዘር ክሬም መሰረታዊ ነግሮች ስለሆኑ በማንኛዉም ብራንድ እና ዋጋ ሚስማማሽን ብትገዢ ምንም አትሆኝም። ነጋዴ ግን የራሱን ለመሸጥ ሊያስፈራራሽ እና ሌላዉን ሊያጣጥል ስለሚችል አትስሚያቸው። ግራ ከገባሽም አማክርሻለሁ

Scroll to Top