ሞይስቸራይዘር ክሬሞች Moisturizers
ከአማዞን ለመምረጥ ከቸኮልሽ ይህን ምረጭ | አማዞን ሊንክ 👉https://amzn.eu/d/0ec9giNC |
ሴራ ቪ / ሴታፊል / ላሮሽ ፖሴይ ውድ ናቸው
ሞይስቸራይዘር ክሬም እና ፀሀይ መከላከያ ሰንስክሪን መሰረታዊ ሁሉ ሊጠቀማቸው ሚገባ ነገሮች ናቸው። የፊትሽን ጤንነት ለመጠበቅ ከፈለግሽ እንዳይደርቅ መጠበቅ አለብሽ። የደረቀ ቆዳ ለመሰባበር፣ ለመሰነጣጠቅ፣ ለመሸብሸብ፣ ለእርጅና በቶሎ ይጋለጣል። ኖርማል ግሪሲሊን እና ቫዝሊን ተቀቢ በተለይ በሙከይፍ ምትተኚ ከሆነ። እንደግሪሲሊን እና ቫዝሊንን እንዳትንቂ። በተለይ ግሪሲሊን ተቀብተሽ በላዩ ላይ ቫዝሊን ከተቀባሽበት ጠዋት ስትነሺ ምርጥ ለስላሳ ፊት ነው ምታገኚው። የግድ በነጋዴ እና ሰው ባለው ሂደሽ መጨናነቅ የለብሽም። ተጨማሪ ቅንጡ ነገር ከፈለግሽ ደግሞ እኔ ይሄው ላማክርሽ ነው ምርጥ የሆኑ አማራጮች
ሞይስቸራይዘር ክሬም ሴራ ቪ በውድ (80 ድርሀም) ከምትገዢ ታዋቂ ምርጥ ለብዙ አመታት ጥቅም ላይ ውሎ የተመሰከረለት ኒቪያ ሶፍት ወይንብ ኒቪያ ብሉ ክሬም ተጠቅመሽ ብርሽን ቆጥቢ። ዋጋው 19 AED አካባቢ ነው ቢበዛ 20 ድርሀም። በፋርማሲ/ሱፐርማርኬት እና ብዙ ገበያዎችም ልታገኚው ትችያለሽ።
ለብራንድ ስም ብዙ ብር ከምታወጪ የሚስማማሽን በጥሩ ዋጋ ፈልገሽ ብትጠቀሚ እና ገንዘብሽን ሌላ ሚጠቅምሽ ነገር ብታዉይው ወይንም ብታጠራቅሚ ጥሩ ነው ዉበትሸን እየጠበቅሽ ማለቴ ነው
ማነጻጸሪያ

ኒቪያ ሶፍት 200ሚሊ 16ድርሃም
ሲምፕል ሞይስቸራይዘር 125 ሚሊ 24 ድርሃም
ኒቪያ ብሉ 400 ሚሊ 16ድርሃም
ሁሉም ኦሪጅናል ሁሉም ታዋቂ ብራንድ ግን ተመጣጣኝ ዋጋ
ሴራቪ ሞይስቸራይዘር ክሬም 500ሚል 80ድርሃም፣ 350ሚሊ 65ድርሃም ፣ ሴታፊል ደግሞ 450ሚሊ 65 ድርሃም
ሚገርመዉ ደግሞ ሴራቪ ፌክ ተመሳስሎ ከምን የተሰራ የማይታወቅ ምርት ዱባይ ላይ መኖሩ ነው
የንጽጽሩ ዉጤት ምንም ማብራሪያ አያስፈልገዉም። ይህን አይተሽ ሴራቪ እንደማያዋጣሽ ካላወቅሽ ፈጣሪ ይርዳሽ። እኔ ኒቬያ ሶፍት የምትለዉን እኔ መክራለሁ ግን ሁሉም ይሆናሉ። ዩሁሉም ሊንክ ከታች። እኔ ምንም ኮሚሽን ወይንም ጥቅም አላገኝም